የሲዳማ ክልል ምክር ቤት  7ኛ መደበኛ ጉባኤ ነገ  ይጀመራል

ሀዋሳ ፤ ሐምሌ 3/2016(ኢዜአ)፦ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 3ኛ ዓመት 7ኛ መደበኛ ጉባኤ ነገ እንደሚመጀር የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ አስታወቁ።

ዋና አፈ ጉባኤዋ ለኢዜአ እንደገለጹት፤  የምክር ቤቱ ጉባኤ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በተለያዩ አጃንዳዎች ላይ ይወያያል።

ከጉባኤው የመወያያ አጀንዳዎች መካከል የ2016  በጀት ዓመት የምክር ቤቱን የአፈጻጸም ሪፖርት እና የ2017 በጀት ዓመት የስራ ዕቅድ በማድመጥ  እንደሚያጸድቅ የሚጠበቅ መሆኑን አስታውቀዋል።

እንዲሁም የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት፣ ለ2017 በጀት ዓመት ዕቅድና  የማስፈጸሚያ በጀት ቀርበው ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ እንደሚጸድቁ አስረድተዋል።

በተጨማሪም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና ኦዲት ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተናግረዋል።

 በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ያሳዩ የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የዕውቅና ሽልማት አሰጣጥ መርሃ ግብር እንደሚኖርም  ዋና አፌ ጉባኤዋ ጠቁመዋል። 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም