በጅግጅጋ እና ሠመራ ዩኒቨርሲቲዎች የማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው

ጅግጅጋ/ሠመራ፤  ሐምሌ 3/2016 (ኢዜአ)፡- በጅግጅጋ እና ሠመራ ዩኒቨርሲቲዎች የማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው።

በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ጠዋት የተጀመረው የማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሠዓትም  እንደቀጠለ ነው።

በዩኒቨርሲቲው ተገኝተው ፈተናውን ያስጀመሩት የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኢብራሂም ኡስማን፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዲላሂ አብዲ አደን እና የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት  በሽር አብዱላሂ (ዶ/ር) ናቸው። 

 ዛሬ በተጀመረው የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ 7ሺህ 592 ተማሪዎችን በማስፈተን ላይ መሆኑም ተገልጿል። 

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናው በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሥር  በአራት ማዕከላት እየተሠጠ እንደሚገኝም ተገልጿል።


 

በሠመራ ዩኒቨርሲቲም በተመሳሳይ ፈተናው እየተሰጠ ነው።

በዩኒቨርሲቲው እየተሰጠ ያለውን የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ያስጀመሩት የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱ ሐሰን እና የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መሐመድ ኡስማን (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ናቸው።

ዛሬ ላይ ፈተናውን እየወሰዱ ያሉት ተማሪዎች 2ሺህ 132  የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች መሆናቸውም ተገልጿል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም