መረጃዎችን  ለመሰበሰብ  የሚረዳ "ሃይ አልቲትዩድ ሳተላይት  ባሉን" ወደ አየር  ተለቀቀ  

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2016(ኢዜአ)፦ የስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢኒስቲትዩት መረጃን ለመሰብሰብ  የሚረዳ "ሃይ  አልቲትዩድ ሳተላይት ባሉን " ወደ አየር  ለቀቀ ።

ሳተላይት ባሉንን የመልቀቅ ስነ ስርአት በሸገር ከተማ  ሱሉሉታ ክፍለ ከተማ  የተካሄደ  ሲሆን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን ዓለማሁ (ዶ/ር)፣ የቦይንግ  ኩባንያ የአፍሪካ  ዳይሬክተር አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ እንዲሁም ተማሪዎች ተገኝተዋል ፡፡

ኢኒስቲትዩቱ  ከቦይንግ  እና ፋሴሳ ከተሰኙ ድርጅቶች ጋር በመተባበር "ፓዝ ወይ ቱ  ስፔስ' በሚል መሪ ሃሳብ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በማስመረቅ ላይ ነው፡፡  

ተማሪዎቹ  ከ 16 እስከ 20 ዓመት  ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን "ሃይ አልቲትዩድ ሳተላይት ባሉን " ዲዛይንና ግንባታ ዙሪያ ለአምስት ወራት ስልጠና የወሰዱ ናቸው፡፡

 ተማሪዎቹ  በስልጠናው የቀሰሙትን  እውቀት  ተጠቅመው የሰሩትን  ሃይ አልቲትዩድ  ሳተላይት ባሉን  የሙከራ ውጤት አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም