አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ  ፈተና  መሰጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2016(ኢዜአ)፦ አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ  ፈተና መሰጠት ጀመረ፡፡

በመላ አገሪቱ የሚሰጠው የ2016 የትምህርት ዘመን አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ዛሬ ተጀምሯል፡፡

ፈተናውን የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአዲስ አበባ  ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ካምፓስ ተገኝተው አስጀምረውታል።


 

ፈተናውን ለመስጠት ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱ መገለጹ ይታወሳል።

የዘንድሮው የ12ኛ አገር አቀፍ ማጠናቀቂያ ፈተና በኦን ላይንና በወረቀት መዘጋጀቱ ይታወቃል።

በኦን ላይን ፈተናውን ለሚወስዱ ተማሪዎች ሰፊ ጊዜ ተሰጥቷቸው ልምምድ ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ፈተናው በዛሬው ዕለት  በመላው አገሪቱ በተመረጡ የመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች በተመሳሳይ ሰዓት መሰጠት ጀምሯል።

ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 3 እስከ 5 ቀን 2016 ዓ.ም የሚወስዱ ሲሆን፥ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ ከሐምሌ 9 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ፈተናውን ይወስዳሉ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ  701 ሺህ 489 ተማሪዎች ብሔራዊ የመልቀቂያ ፈተናውን እንደሚወስዱ ትምህርት ሚኒስቴር መግለጹ ይታወቃል። 

 
 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም