አፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ በቀድሞ የአሜሪካ ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለፁ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2016(ኢዜአ)፦ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ በቀድሞ የአሜሪካ ሴናተር ጂም ኢንሆፎ   ህልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገልፀዋል።

አፈ ጉባኤው በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሐዘን መልዕክት ሴናተር ጂም ኢንሆፍ በደስታም ሆነ በችግር ጊዜ እውነተኛ  የኢትዮጵያ ወዳጅ እንደነበሩ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም