ቀጥታ፡

4 ነጥብ 6 ኪሎ ግራም ወርቅ በሕገ-ወጥ መንገድ ጭኖ ሲንቀሳቀስ የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 2/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ 4 ጥብ 6 ኪሎ ግራም ወርቅ በሕገ-ወጥ መንገድ ጭኖ ሲንቀሳቀስ የነበረን ተጠርጣሪ ከነ-ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገለፀ።

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓ.ም በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ከተማ 02 ቀበሌ ኮድ 2 አ.አ የሰሌዳ ቁጥር 32808 ሀይሉክስ መኪና 4 ነጥብ 6 ኪሎ ግራም ወርቅ ጭኖ ሲንቀሳቀስ የፌዴራል ፖሊስ ኮንትሮባንድ ቁጥጥር መምሪያ ከኢትዮጵያ ጉሙሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ባደረጉት ክትትል መሆኑ ተገልጿል።

ኅብረተሰቡ ህገ-ወጥ የወርቅ ንግድንና ዝውውር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት በውል በመገንዘብ በመሰል ተግባር ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና ቡድኖችን ሲመለከት የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp) በመጠቀም ወይም በ991 ነፃ የስልክ መስመር በመደወል ወይም መልዕክት በመላክ ጥቆማ እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም