ቀጥታ፡

እግር ኳሳችንን ወደ ክብሩ ለመመለስ ከስፖርት ቤተሰቡ ጋር በቅርበት መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 1/2016(ኢዜአ)፦እግር ኳሳችንን ወደ ክብሩ ለመመለስ ከስፖርት ቤተሰቡ ጋር በቅርበት መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለከንቲባ አዳነች አቤቤ የዕውቅና ሽልማት ሲያበረክት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የበላይ ጠባቂ አድርጎ ሰይሟል።

ይሔንን ተከትሎም ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አዲስ አበባ ላይ እየሰራን ያለውን የስፖርት መሠረተ ልማት መስፋፋት በተለይም የእግር ኳስ ሜዳዎችን በማየት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሰጠኝ እውቅና እንዲሁም የዋልያዎቹና የሉሲዎቹ የበላይ ጠባቂ አድርጎ ሃላፊነት ስለሰጠኝ ከልብ አመሰግናለሁ ሲሉ ገልጸዋል።


 

የእግር ኳስ ስፖርት ሕዝባችን በስስት የሚያየውና ታሪካችንም ከጀማሪዎቹ ፣ ነገር ግን በውጤት ከኃላ የቀረን እና የስፖርት ቤተሰቡን እያስቆጨ የሚገኝ ቢሆንም ይህን ታሪክ ለመቀየር በጋራ በመስራት እግር ኳሳችንን ወደ ክብሩ ለመመለስ ከስፖርት ቤተሰቡ ጋር በቅርበት መስራታችንን አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም