አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው - ኢዜአ አማርኛ
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው
አሶሳ፤ ሐምሌ 1/2016(ኢዜአ)፦ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው።
የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክተር እና የፈተና ማዕከል ግብረ ኃይል አስተባባሪ ዶክተር ወንድም መኩሪያው ለኢዜአ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው ከሐምሌ 3 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው።
በዩኒቨርሲቲው በአጠቃላይ የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ፈተናዎችን የሚወስዱት ከ10 ሺህ 300 በላይ ተማሪዎች እንደሆኑ ገልጸው፤ አሁን የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞችን ነው በመቀበል ላይ የምንገኘው ብለዋል።
ፈተናውን ስኬታማ ለማድረግ አራት ግብረ ሃይሎች ተቋቁመው መኝታ፣ ምግብ እና ሌሎች ግብዓቶችን በማሟላት ለተማሪዎቹ አቀባበል እየተደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ከ280 በላይ ፈታኞች ዝግጅት ማድረጋቸውንም ዶክተር ወንድም መኩሪያው ገልጸዋል።