ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአራት ኪሎ-ቀበና-ኬንያ ኤምባሲ ኮሪደር ሥራ መጠናቀቁን አበሰሩ 

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 1/2016 (ኢዜአ)፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአራት ኪሎ-ቀበና-ኬንያ ኤምባሲ ኮሪደር ሥራ መጠናቀቁን አበሰሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት የአራት ኪሎ-ቀበና-ኬንያ ኤምባሲ ኮሪደር ሥራ መጠናቀቁን ገልጸው፤ አካባቢውን አረንጓዴ የማድረግ ጥረቱ በጉልህ ይታያል ብለዋል። 


 

ባለፉት ሳምንታት የምሽቱን ውበት እንዳደነቅነው ዛሬ ደግሞ የማለዳን እይታ በኮሪደር ልማታችን ተመልክተናል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለስኬቱ በሥራው ለተሳተፉት የከተማው አስተዳደር እና በሙሉ ፈቃድ ለተሳተፉ የግሉ ሴክተር ምስጋና አቅርበዋል በመልዕክታቸው። 

የከተማችንን የመኪና ማቆሚያ እጥረት የሚቀርፉ የፓርኪንግ ቦታዎች ተገንብተዋል ሲሉም ነው የገለጹት።


 

 የእግር ጉዞን የሚያበረታቱ የእግረኛ መንገዶች ተስፋፍተው መሰራታቸውንም ጠቁመዋል። 

ይህን ባሕል መንከባከብ እና ማሳደግ ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ሁላችንም ህልውና ለሆነው አዲስ መልክ ጠባቂዎች መሆን አለብን ሲሉ አሳስበዋል።
 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም