ሰላም ለመሆን ብቸኛው እና አማራጭ የሌለው መንገዳችን ሰላም እራሱ ነው - አቶ ብናልፍ አንዱአለም - ኢዜአ አማርኛ
ሰላም ለመሆን ብቸኛው እና አማራጭ የሌለው መንገዳችን ሰላም እራሱ ነው - አቶ ብናልፍ አንዱአለም

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 30/2016(ኢዜአ)፦ ሰላም ለመሆን ብቸኛው እና አማራጭ የሌለው መንገዳችን ሰላም እራሱ በመሆኑ፤ ለሰላም የማንከፍለው መስዋዕትነት የለም ሲሉ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱአለም ገለጹ።
ሚኒስትሩ ዛሬ በ33 የተመረጡ ከተሞች “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም”” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሔደው ሀገር አቀፍ ሩጫ ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።
ዛሬ በሁሉም ሀገሪቱ ክፍል አዲስ አበባን ጨምሮ በሰላሳ ሶስት የተመረጡ ከተሞች "ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ሀገር አቀፍ ሩጫ እኛ ኢትዮጵያውያን ለሰላም ያለንን ቁርጠኝነት ለመላው አለም አሳይተናል ሲሉም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ሰላም ለመሆን ብቸኛው እና አማራጭ የሌለው መንገዳችን ሰላም እራሱ በመሆኑ፤ ለሰላም የማንከፍለው መስዋዕትነት እንደሌለ በተግባር ላሳያችሁ ድንቅ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ሲሉም ተናግረዋል።
ሁሉም የሀገራችን ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ለሀገራችን ሰላም ያሳዩትን ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት እንደሚያደንቁ የገለጹት ሚኒስትሩ ሰላሟ የበዛና የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል ዛሬም ነገም በትጋት እና በጋራ እንሰራለን ብለዋል።