ቀጥታ፡

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በደብረ ብርሀንና አሰላ መምህራን ትምህርት ኮሌጆች ያሰለጠናቸውን የቅድመ መጀመሪያ ትምህርት መምህራንን አስመረቀ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 30/2016 (ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በደብረ ብርሀንና አሰላ መምህራን ትምህርት ኮሌጆች ያሰለጠናቸውን ከ2 ሺህ በላይ የቅድመ መጀመሪያ ትምህርት መምህራንን አስመረቀ።

ቢሮው ከደብረ ብርሀንና አሰላ መምህራን ትምህርት ኮሌጆች ጋር ውል በመግባት የቅድመ መጀመሪያ ትምህርት መምህራንን ማስልጠኑ ተገልጿል፡፡

በዛሬው እለትም 2ሺህ 27 መምህራን በዲፕሎማ ተመርቀዋል።


 

በምረቃ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመራቂዎች በስልጠና ያገኙት ዕውቀት ከራሳቸው ፈጠራ ጋር በማዘመድ ብንቁ ዜጋ የማፍራት ኃላፊነታቸው በአግባቡ እንዲወጡ ጠይቀዋል።

ከተማ አስተዳደሩ የቀዳማይ ልጅነት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን አንስተው፤ ሰልጣኞችም ይህን ታሳቢ በማድረግ ብቁ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመገንባት የሚከናወነውን ስራ በማገዝ ረገድ የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም