ሀረር ለረጅም ዓመታት የምታወቅባቸውን የሰላም፤ የአብሮነትና የመቻቻል እሴቶቿን መጠበቅ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ - ኢዜአ አማርኛ
ሀረር ለረጅም ዓመታት የምታወቅባቸውን የሰላም፤ የአብሮነትና የመቻቻል እሴቶቿን መጠበቅ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ
ሀረር፤ ሰኔ 30/2016 (ኢዜአ)፦ ሀረር ለረጅም ዓመታት የምታወቅባቸውን የሰላም፤ የአብሮነትና የመቻቻል እሴቶቿን መጠበቅና ማስቀጠል ይገባል ሲሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ።
በሀረር ከተማ "ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም" በሚል መሪ ሀሳብ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሂዷል።
የጎዳና ላይ ሩጫውን በንግግር ያስጀመሩት ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ሰላም ለሰው ልጆች የመኖር ህልውና መሰረት መሆኑን ጠቁመዋል።
የሩጫ መርሀ ግብሩ በተለይ ሀረር የምትታወቅበትን የሰላም፣ የመቻቻልና የአብሮነት እሴቶች የበለጠ የሚጠናከሩበት መሆኑን ገልፀዋል።
ሰላምና የህግ የበላይነት ከሌለ የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አይቻልም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለሰላም ልዩ ትኩረት ተሰቶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በተለይ ህብረተሰቡ ሀረር ለረጅም ዓመታት የምታወቅባቸውን የሰላም፤ የአብሮነትና የመቻቻል እሴቶቿን መጠበቅና ማስቀጠል እንደሚጠበቅ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የጎዳና ላይ ሩጫው ላይ የክልሉ አመራሮች፣ ዳያስፖራዎች እንዲሁም የክልሉ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
ውድድሩን ከ 1 እስከ 3 በመውጣት ያጠናቀቁ ተወዳዳሪዎች ከርዕሰ መስተዳድሩ እጅ የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲን፣ የሀረሪ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ፣ የሀረሪ ጉባኤ አፈጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች መገጠታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።