ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ከሁሉም በላይ ሰላም ያስፈልጋታል-አቶ ብናልፍ አንዱለም   

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 30/2016 (ኢዜአ)፦  በአዲስ አበባ "ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም" በሚል መሪ ሀሳብ አገር አቀፍ የሰላም ሩጫ ውድድር ተካሄዷል።

"ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም" በሚል መሪ ሀሳብ የሰላም የሩጫ 

ውድድሩ የተዘጋጀው በሰላም ሚኒስቴር እና በአጋር አካላት ትብብር ነው።


 

በውድድሩ  የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱአለም፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች የፌደራል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ ታዋቂ አትሌቶችና ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ አገራት ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል።

በዚሁ ወቅት የሰላም ሚንስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱአለም ኢትዮጵያ ከሁሉም በላይ ሰላም ያስፈልጋታል ብለዋል።

የሰላም ሩጫው ዋና አላማ የሰላም ፍላጎታችንን ከፍ አድርገን ለማሳየት ነው በማለት ጨምረው ገልጸዋል።

ሰላም የሁለም መሰረት ነው ያሉት ሚኒስትሩ በመሆኑም ሁላችንም ለሰላም በሰላም መተባበር አለብን ሲሉ ተናግረዋል።


 

ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች እያሳካቻቸው ያሉትን ስኬቶች ለማስቀጠል፤ ሰላም በእጅጉ ያስፈልጋታል ነው ያሉት።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው፣ የከተማችን ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ የተጠበቀው ህዝብን ያሳተፈ የሰላም ስራ በመሰራቱ ነው ብለዋል።

በመሆኑም ይህን ሰላም አስጠብቆ ለመዝለቅ ሁሉም ሰው እያበረከተ ያለውን ድርሻ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በአገር አቀፍ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር በመላው የኢትዮጵያ ክፍል የሚገኙ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ተሳትፈዋል።

ውድድሩ ዛሬ በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ እና በሌሎች ዋና ዋና ከተሞች በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የሩጫው ዓላማ ስለ ሰላም ግንዛቤ መፍጠርና ዜጎች ለዘላቂ ሰላም የበኩላቸውን ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው ለማሳሰብ ነው።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም