የመጀመሪያው የኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን የጋራ ድንበር አስተዳዳሪዎች ስብሰባ ተጠናቀቀ - ኢዜአ አማርኛ
የመጀመሪያው የኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን የጋራ ድንበር አስተዳዳሪዎች ስብሰባ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 28/2016(ኢዜአ)፦ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን የጋራ ድንበር አስተዳዳሪዎች ስብሰባ ስኬት መጠናቀቁ ተገለጸ።
የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮች አገራቱ የጋራ ድንበር አስተዳደር ስብሰባ ማካሄዳቸውን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በዚህም የሁለቱ ሀገራት የህዝብ ለህዝብና የንግድ ግንኙነት፣ እንዲሁም ሰላምና ደህንነትን በጋራ የማስጠበቅ ተግባራቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።
ድንበር ተሻጋሪ ደህንነትን እና የጋራ ልማትን ለማጎልበትም መግባባት ላይ መደረሱ ተገልጿል።
በውይይቱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፣ የደቡብ ሱዳን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ማንዴ ሴማይ ኩምባ፣ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡመድ ኡጁሉ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፣ የደቡብ ሱዳን የክልል አስተዳዳሪዎችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።