ቀጥታ፡

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን የጋራ ድንበር አስተዳዳሪዎች የምክክር መድረክ ተጀመረ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 27/2016(ኢዜአ)፦ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን የጋራ ድንበር አስተዳዳሪዎች የምክክር መድረክ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ተጀምሯል።

ለሁለት ቀናት የሚቆየው መድረክ በልማት ትብብር፣ በጋራ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማሳደግ ላይ ሀሳብ ለመለዋወጥ ያለመ ነው።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ፍስሃ ሻውል በመድረኩ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፣ ለድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች የጋራ መፍትሄ በማስቀመጥ የሁለቱን ወንድማማች ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።


 

በደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የድንበር እና የውጭ ዜጎች ጉዳይ ዳይሬክተር አምባሳደር አንቲፓስ ኒዮክ በበኩላቸው፣ መድረኩ የጋራ ተጠቃሚነትን መንፈስ በማጎልበት የጋራ ጉዳዮችን ለመፍታት ጠቀሜታ እንዳለው መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም