የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ 8 ተደለደለች - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ 8 ተደለደለች
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 27/2016(ኢዜአ፦ኢትዮጵያ በሞሮኮ አስተናጋጅነት በሚካሄደው 35ኛ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ 8 ከጊኒ፣ታንዛንያና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ተደልድላለች።
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን(ካፍ) የ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ድልድል የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ አድርጓል።
በዚሁ መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድብ 8 ከጊኒ፣ታንዛንያና ዴሞክራሲ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ተደልድላለች።
በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ 48 አገራት በ12 ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የማጣሪያ ጨዋታዎች በመስከረም ወር 2017 ዓ.ም ይጀምራሉ።
በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 24 አገራት ይሳተፋሉ።