ለኢትዮጵያዊያን የሚያስፈልጉ ስድስቱ “መ” ዎች:- - ኢዜአ አማርኛ
ለኢትዮጵያዊያን የሚያስፈልጉ ስድስቱ “መ” ዎች:-
1) መወያየት- ችግሮችን ከግጭት ይልቅ በውይይት መፍታት
2) መትከል- ከችግኝ ባሻገር ለኢትዮጵያ የሚበጁ ተቋማትን በመትከል ሀገርን ማጽናት
3) መታደስ- እሳቤዎቻችንና አኗኗራችንን ወቅቱን በዋጀ መልኩ ማደስ
4) መሰብሰብ- ግብርን ጨምሮ ለህዝብ ጥቅም የሚውሉ ገቢዎችን መሰብሰብ
5) መነጠል- ከክፉ ሃሳብን፣ ከዘረኝነት እና ከሰፈርተኝነትን መነጠል
6) መዘጋጀት- አሁናዊ ሁኔታዎችን በሚዋጅ መልኩ ጠንካራ የመከላከያ ኃይል ማዘጋጀት ፤ ለዚህ ደግሞ እርስ በርስ ማገር በመሆን አገርን ማጠናከር፡፡