በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት የጋራ ድላችን ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት የጋራ ድላችን ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 27/2016(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት የጋራ ድላችን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት የጋራ ድላችን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የከተማዋን ገፅታ የቀየረ አስደማሚ ፕሮጀክት መሆኑን ተናግረዋል።
በፕሮጀክቱ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን ጠቅሰው ልማቱ የአረንጓዴ ልማትንና የዜጎች መዝናኛን ያካተተ በመሆኑ ጠቀሜታው የላቀ ነው ብለዋል።
በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለው የኮርደር ልማት በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጠቆሙት።
በፕሮጀክቱ ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ላበረከቱና እያበረከቱ ላሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።