ቀጥታ፡

በግጭት፣ በጦርነትና በመፈንቅለ መንግስት ፈፅሞ ስልጣን መያዝ አይቻልም- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 27/2016(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ በግጭት፣ በጦርነትና በመፈንቅለ መንግስት ፈፅሞ ስልጣን መያዝ አንደማይቻል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮችና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም በለውጡ ታግለን ላመጣነው ፍሬ ክብር በመስጠት ለቀረው በጋራ መስራት አለብን ሲሉ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ዋልታ ረገጥ እሳቤ ሁላችንንም እየጎዳ በመሆኑ መቅረት አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይትና ምክክር ለጋራ መፍትሄ መስራት አለብን ብለዋል።

በኢትዮጵያ በግጭት፣ በጦርነትና በመፈንቅለ መንግስት ፈፅሞ ስልጣን መያዝ አይቻልም፤ በመሆኑም የልማት ህልሞቻችንን ለማሳካት በጋራ እንስራ ሲሉ ጠይቀዋል።

እየተዋጋን ያለነው በአባቶቻችን ጠብ በመሆኑ እርስትም ጦርነትም ወርሰን ወደ ፊት መራመድ እንቸገራለን ሲሉ አስገንዝበዋል። 

በመሆኑም በየትኛውም አካባቢ ነፍጥ ይዘው የሚንቀሳቀሱ አካላት ከጠብመንጃ ወደ ጠረንጴዛ ይምጡ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከማንም ጋር ለምክክር ዝግጁ ነው ሲሉም አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም