ቀጥታ፡

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ተደርጓል - የፀጥታና ደኀንነት የጋራ ግብረ ኃይል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 27/2016(ኢዜአ)፦ የፀጥታና ደኀንነት የጋራ ግብረ ኃይል ከሐምሌ 3 እስከ 11/2016 ዓ.ም የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገለፀ።

ተማሪዎች የለፉበትን የትምህርት ውጤት ማግኘት ይችሉ ዘንድ ፈተናው ያለምንም የፀጥታ ችግር በስኬት እንዲጠናቀቅ የጋራ ግብረ ኃይሉ ለፈተና ቁሳቁሶች እጀባ፣ ጥበቃ እና ፍተሻ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ኅብረተሰቡም ይህንን አውቆ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግና አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከት የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ባዘጋጀው የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ(EFPApp) በመጠቀም ወይም በ991 ነፃ የስልክ መስመር በመደወልና መረጃ በመላክ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት በአካል ጥቆማ በመስጠት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ግብረ ኃይሉ ጥሪ ማቅረቡን የፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም