የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 27/2016(ኢዜአ)፦የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 36ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል።

ምክር ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ረቂቅ በጀትን አስመልክቶ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ አዳምጦ ረቂቅ በጀቱን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩም በፌዴራል መንግሥቱ የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ።

በስብሰባው ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ።

የስብሰባው ሙሉ ሂደትም በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የሚተላለፍ መሆኑን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም