በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀድያ ሆሳዕና ኢትዮጵያ ቡና አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀድያ ሆሳዕና ኢትዮጵያ ቡና አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 26/2016(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሆሳዕና ኢትዮጵያ ቡናን 2 ለ 1 በማሸነፍ የውድድር ዓመቱን የመጨረሻ ጨዋታ በድል አጠናቋል።
በሃዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ በተካሄደው ጨዋታ አጥቂው የኋላሸት ሰለሞን በ18ኛው እና 36ኛው ደቂቃ ያስቆጠራቸው ግቦች ሀድያ ሆሳዕናን አሸናፊ አድርጓል።
የፊት መስመር ተሰላፊው አንተነህ ተፈራ በ2ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ግብ ኢትዮጵያ ቡናን ከሽንፈት አልታደገም።
ውጤቱን ተከትሎ ሀድያ ሆሳዕና በ41 ነጥብ ከነበረበት 10ኛ ደረጃ ወደ 9ኛ ከፍ ብሏል።
ኢትዮጵያ ቡና በ51 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በ30ኛ ሳምንት የመጀመሪያው ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ ወላይታ ድቻን 2 ለ ዐ አሸንፏል።