ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከማርዮት ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንትና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከማርዮት ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንትና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 26/2016(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት የማርዮት ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንት እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አንቶኒ ካፑአኖ ጋር ተገናኝተው በማደግ ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ የጉዞ እና የሆስፒታሊቲ ዘርፍ ላይ ተወያይተዋል።
በውይይቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባህል ሀብቷ እና ታሪካዊ ቅርስ ይዞታዋ ብሎም በአስደናቂ የመልክዓ ምድር ገፅታዋ የታወቀችው ኢትዮጵያ የቱሪዝም ኢንደስትሪዋን በማስፋፋት ላይ አተኩራለች ማለታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በአለም ዙሪያ 8785 ያህል ቅርንጫፎች እና የሀብት አድራሻዎች በመያዝ በመስተንግዶ እና ማረፊያ አገልግሎት ዘርፍ መሪ የሆነው ማሪዮት ኢንተርናሽናል በዚህ ስራ ጉልህ ሚና ለመጫወት ትልም ይዟል።