በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የመክፈቻ ጨዋታዎች ላይ የመጫወቻ ሜዳና የሰዓት ለውጥ ተደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የመክፈቻ ጨዋታዎች ላይ የመጫወቻ ሜዳና የሰዓት ለውጥ ተደረገ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25/2016(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የመክፈቻ ጨዋታዎች ላይ የመጫወቻ ሜዳና የሰዓት ለውጥ ማድረጉን የፕሪሚየር ሊጉ ውድድርና ስነ ስርዓት ኮሚቴ አስታወቀ።
በ30ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ውሎ ረቡዕ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ሃዋሳ ከተማ ከወላይታ ድቻ ከቀኑ 9 ሰዓት እንዲሁም ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮዮጵያ ቡና ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን እንዲያደርጉ መርሐ ግብር ወጥቶላቸው ነበር።
ይሁንና የመክፈቻ ጨዋታዎቹ የቀጥታ ሽፋን እንደሌላቸውና በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ሊካሄዱ የነበሩት ጨዋታዎች በአስገዳጅ ምክንያት ወደ ሀዋሳ ሰው ሰራሽ ሜዳ መቀየራቸውን የፕሪሚየር ሊጉ ውድድርና ስነ ስርዓት ኮሚቴ ገልጿል።
በዚሁ መሰረት ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ሃዋሳ ከተማ ከወላይታ ድቻ ከቀኑ 7 ሰዓት እንዲሁም ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮጵያ ቡና ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል።