ቀጥታ፡

የምሥራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል ልዑክ በኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል ሞተራይዝድ ሻለቃን ጎበኘ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25/2016(ኢዜአ)፦  የምሥራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል ልዑክ በኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል ሞተራይዝድ ሻለቃን ጎበኘ። 

በኬኒያ ናይሮቢ ከሚገኘው የምሥራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል ቢሮ የተውጣጣ ልዑክ ኢትዮጵያን ለምሥራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል የምታዋጣውን ሞተራይዝድ ሻለቃ የግዳጅ ዝግጁነት የሚያረጋግጥ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ይታወቃል።


 

በምሥራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀኔራል ፖል ካሁሪያ ጀማ የተመራው የተጠባባቂ ኃይሉ ልዑክ በኢትዮጵያ ቆይታው ቢሸፍቱ የሚገኘውን የኢትዮጵያን የምሥራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል ሞተራይዝድ ሻለቃ ጠቅላይ ጦር ሰፈር ተገኝቶ የሻለቃዋን ዝግጁነትና አጠቃላይ አቁመና ተመልክቷል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም