ቀጥታ፡

ኢንስቲትዩቱ በተቋሙ ለበለፀጉ አራት የፈጠራ  ውጤቶች ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን የፓተንት መብት  ተሰጠው

 አዲስ አበባ፤ ሰኔ 24/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩቱ በተቋሙ ለበለፀጉ አራት የፈጠራ ውጤቶች ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን የፓተንት መብት ማግኘቱን አስታወቀ።

ለኢንስቲትዩቱ የተሰጠው የፓተንት መብት ሰው ሰራሸ አስተውሎት ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረጉ የስኳር በሽታ አይነት የሚለይ ፣ የጡት ካንስር አይነት የሚለይ፣ የህፃናት የቆዳ በሽታ ልየታ የሚሰራ ሥርዓት ና  የቡና ቅጠል በሽታ ልየታ የሚያደርግ የፈጠራ ውጤቶች እንደሆኑ ተገልጿል።


 

የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር  ዶክተር ኢንጂነር ወርቁ  ጋቸና  ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ወልዱ ይመስል የፓተንት መብት የእውቅና ሰርተፍኬት ተቀብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም