በተለያዩ የዓለም አገራት የሚኖሩ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገር ቤት እየገቡ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በተለያዩ የዓለም አገራት የሚኖሩ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገር ቤት እየገቡ ነው
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 24/2016 (ኢዜአ)፦ በተለያዩ የዓለም አገራት የሚኖሩ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገር ቤት እየገቡ ነው ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ታህሳስ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገር ቤት እንዲመጡ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡
የጥሪው ዋነኛ ዓላማም የሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን የአገራቸውን ባህል፣ ታሪክና እሴቶች በአግባቡ እንዲገነዘቡ ለማድረግ ነው።
በዚህም መሰረት ከዚህ ቀደም በሁለት ዙሮች የገቡ ሀገራቸውን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን የሶስተኛው ዙር ጎብኝዎችም ለተመሳሳይ ዓላማ ወደ ሀገር ቤት መግባት ጀምረዋል።
በዛሬው ዕለትም በተለያዩ የዓለም አገራት የሚኖሩ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ሲገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያዊያኑ በቆይታቸው በተለያዩ የሀገሪቷ አካባቢዎች በመዘዋወር የልማት ስራዎችንና የቱሪዝም መስህቦችን የሚጎበኙ ይሆናል።