ቀጥታ፡

በ26ተኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን ለመሳተፍ የመጡ በርካታ ዲያስፖራዎች አቀባበል ተደረገላቸው

ሀረር፤ ሰኔ 23/2016( ኢዜአ) ፦ ከቀናት በኋላ በሀረር ከተማ በድምቀት በሚከበረው 26ተኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን ለመሳተፍ የመጡ በርካታ ዲያስፖራዎች በድሬደዋ ኤርፖርት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።


 

እንግዶቹ ድሬደዋ አየር ማረፊያ ሲደርሱም የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመርን ጨምሮ በሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ነው አቀባበል የተደረገላቸው።

26ኛው አለም አቀፉ የሀረር ቀን ከቀናት ቡኋላ በተለያዩ መርሀ ግብሮች በታላቅ ድምቀት ይከበራል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም