ቀጥታ፡

የቀድሞ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮከብ ተጫዋቾች የህዳሴ ግድብን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 22/2016(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ የሚገኙት የአፍሪካ የቀድሞ ኮከብ እግር ኳስ ተጫዋቾች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱም የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ እና የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብረሀም በላይ (ዶ/ር) ስለግንባታ ሂደቱና ፕሮጀክቱ ለኢትዮጵያውያን ስላለው ትርጉም ገለፃ ማድረጋቸውን ከቱሩዝም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።


 

ናይጀሪያዊያኑ የቀድሞ የእግር ኳስ ከዋክብት ኑዋንኮ ካኑና ዳንኤል አሞካቺ፣ እንዲሁም ሴኔጋላዊው ሄንሪ ካማራን ጨምሮ የኪነጥበብ ባለሙያዎችና የፋሽን ዲዛይነሮች በጉብኝቱ ከተሳተፉት መካከል እንደሚገኙበትም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም