ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የዘንድሮን የአረንጓዴ አሻራ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 22/2016(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ሀይቅ ከተማ የዘንድሮን የአረንጓዴ አሻራ ዛሬ አስጀምረዋል።


 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ሀይቅ ከተማ የዘንድሮን የአረንጓዴ አሻራ አስጀምረናል ብለዋል።

እኛ ስንተክል ሀገርን አረንጓዴ እያለበስን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች ጉልበት እየጨመርን ነው ሲሉም ገልጸዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም