ቀጥታ፡

ዶክተር ዓለሙ ስሜ ከኬንያ መንገድ እና ትራንስፖርት ካቢኔ ፀሃፊ ኪፕቹምባ ሞርኮሜን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 22/2016(ኢዜአ)፦ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) ከኬንያ መንገድ እና ትራንስፖርት ካቢኔ ፀሃፊ ኪፕቹምባ ሞርኮሜን ጋር በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ በኬንያ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ጉዳዮች ላይ የተወያዩ ሲሆን፣ በተለይም ሁለቱን ሀገራት በመሰረተ ልማት ማስተሳሰር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ እና በኬንያ መካከል የንግድ፣ የኢኮኖሚ ዕድገት እና የጋራ ትብብርን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ማድረጋቸውም ተገልጿል፡፡

በውይይቱ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ መሳተፋቸውን ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም