ቀጥታ፡

በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 5 ወርቅ፣ 4 የብርና 1 የነሐስ ሜዳልያ በማሸነፍ ውድድሩን አጠናቀቀች

አዲስ አበባ ሰኔ 20/2016(ኢዜአ)፦በ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 5 ወርቅ፣ 4 የብርና 1 የነሐስ ሜዳልያ በማሸነፍ ውድድሩን አጠናቃለች።

በካሜሩን ዱዋላ አስተናጋጅነት በተካሔደውና ከ27 ሃገራት በላይ የተውጣጡ 2500 አትሌቶች ላለፉት 6 ቀናት ሲሳተፉበት የነበረው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር በደማቅ ስነ-ስርዓት ተጠናቋል።


 

ኢትዮጵያም በ32 ሴት እና በ36 ወንድ አትሌቶች በ19 የአትሌቲክስ የውድድር አይነቶች በመሳተፍ በ5 የወርቅ፣ በ4 ብር እና በአንድ የነሐስ በድምሩ 10 ሜዳልያዎች በማሸነፍ አጠናቃለች።

በውድድሩ ላይ የወርቅ ሜዳልያ ያስገኙ አትሌቶች፦

👉ፋንታዬ በላይነህ በ5ሺ ሜትር ሴቶች

👉ንብረት መላክ በ10ሺ ሜትር ወንዶች

👉ምስጋና ዋቁማ በወንዶች በ20 ኪሎ ሜትር እርምጃ

👉 ስንታየሁ ማስሬ በሴቶች በ20 ኪሎ ሜትር እርምጃ

👉ሳሮን በርሄ በ1500 ሜትር ሴቶች

የብር ሜዳልያ ያስገኙ አትሌቶች፦

👉ውብርስት አስቻል በ5ሺ ሜትር ሴቶች

👉ገመቹ ዲዳ በ10ሺ ሜትር ወንዶች

👉አለምናት ዋለ በ3ሺ መሠናክል ሴቶች

👉አትሌት ንብረት መላክ በ5ሺ ሜትር ወንዶች የብር ሜዳልያ በተጫማሪ አስገኝቷል።

የነሐስ ሜዳልያ ያስገኘችው አትሌት፦

👉አትሌት ገላ ሀምበሴ በ10ሺ ሜትር ሴቶች የነሐስ ሜዳልያ አስገኝታለች፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም