ሐረር ቀጣይ ሳምንት ለሚከበረው የ26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን እያሸበረቀች ትገኛለች - ኢዜአ አማርኛ
ሐረር ቀጣይ ሳምንት ለሚከበረው የ26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን እያሸበረቀች ትገኛለች
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 19/2016(ኢዜአ)፦ የዘንድሮው 26ኛው አለም አቀፍ የሐረር ቀን የሚከበርባት ሐረር ከተማ በዓሉን ለማክበር ከወትሮው በተለየ መልኩ እየተዘጋጀችና እያሸበረቀች እንደምትገኝ ተገለጸ።
በሐረር ከተማ በተለይም አሁን ላይ በየዘርፉ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች የከተማዋን ትንሳዔ የሚያበስሩ፤ ከፍታዋን የሚያረጋግጡና ታላቅነቷን የሚመሰክሩ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙም ተመላክቷል።
በዓሉ በከተማው መከበሩም እነኚህ ስራዎች የበለጠ እንዲጠናከሩ እያስቻለ እንደሚገኝም ተጠቅሷል።
ሁሌም ቢሆን ለሐረር ያለው ፍቅር የማይነጥፈው በተለያየ የአለም ክፍሎች የሚገኘው ሐረሪ እና የሐረር ተወላጅ ወደ ከተማዋ በመምጣት በዓሉን በጋራ እንዲያከብርና ናፍቆቱን እንዲወጣ በዓሉ ምቹ አጋጣሚ የሚፈጥር ነው።
የምስራቅ ኢትዮጵያዊ ፈርጥ ከተማ ሐረር እንደ ስሟ አበባ መስላ፤ የሰላም አየር እየተነፈሰች፤ በደስታና በናፍቆት ልጆቼ እንኳን ደህና መጣችሁ ብላ ልትቀበላችሁ ቅድመ ዝግጅቶቿን አጠናቃ የምትጠብቃቸው መሆኗንም በመረጃው ተገልጿል።