ኢትዮጵያ በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮናው አምስተኛ የወርቅ ሜዳሊያዋን አግኝታለች

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 19/2016(ኢዜአ)፦በካሜሮን ዱዋላ እየተካሄደ በሚገኘው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና አትሌት ሳሮን በርሄ ለኢትዮጵያ በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች።

በዚህም ኢትዮጵያ በውድድሩ ያገኘችውን የወርቅ ሜዳሊያ ወደ አምስት ከፍ አድርጋለች።

ዛሬ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል የሴቶች ፍጻሜ ውድድር አትሌት አለምናት ዋለ የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።

23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ማምሻውን ይጠናቀቃል።

በውድድሩ መዝጊያ በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ፍጻሜ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉበት ውድድር ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ እስከ አሁን በተሳተፈችባቸው ውድድሮች 5 የወርቅ ፣ 3 የብር እና 1 የነሐስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም