በኮትዲቯር በደረሰ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ የ24 ሰዎች ህይወት አለፈ

 

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 18/2016 (ኢዜአ)፦በኮትዲቯር ትልቋ የኢኮኖሚ ከተማ አቢጃን በተከሰተ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ የ24 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነገረ።

በምዕራብ አፍሪካ ሃገራት ከመደበኛው ከፍ ባለ መልኩ እየጣለ ያለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በኢኮኖሚ ከተማዋ አቢጃን ባለፉት 10 ቀናት በተከታታይ የጣለው ዝናብ የተፈጥሮ አደጋዎችን አስከትሏል።

በዚህም በመላው ሃገሪቱ ያሉ የውሃ አካላት ከፍታ የጨመረ ሲሆን የጎርፍ መጥለቅለቅና የመሬት መንሸራተትም ተከስቷል።

ዝናቡ ባስከተለው ጎርፍና የመሬት መንሸራተት አደጋም 24 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

ከአደጋው ጋር በተያይዘ ሁለት ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን ያመለከተው የሲጂቲኤን ዘገባ በክስተቱ የህንጻዎች መደርመስ አደጋ ሊያጋጥም እንደሚችል ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን አስነብቧል።

ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት በሚቆየው የሀገሪቱ የክረምት ወቅት አስቸጋሪ የተፈጥሮ ክስተት ሊያጋጥም እንደሚቸልም በዘገባው ተመልክቷል።

May be an image of 3 people and body of water

All reactions:

127127

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም