አሸባሪው ሸኔ በየትኛውም መመዘኛ የኢትዮጵያ ስጋት ወደማይሆንበት ደረጃ ደርሷል - ሌተናል ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋ - ኢዜአ አማርኛ
አሸባሪው ሸኔ በየትኛውም መመዘኛ የኢትዮጵያ ስጋት ወደማይሆንበት ደረጃ ደርሷል - ሌተናል ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 18/2016(ኢዜአ)፦ በመከላከያ ሠራዊታችን ተከታታይ ምት ዛሬ ላይ አሸባሪው ሸኔ በየትኛውም መመዘኛ የኢትዮጵያ ስጋት ወደማይሆንበት ደርሷል ሲሉ የደቡብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋ ገለፁ።
የአርሲ ዞን አሁናዊ የሠላም ሁኔታ በሚመለከት ከዞኑ አባ ገዳዎች፣ አደ ሲንቄዎች እና ከልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ዋና አዛዡ ውይይት አድርገዋል።
በሰሜን ጎጃምና በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ኮማንድ ፖስት የተሰማራው ኮር በጽንፈኛው ቡድን ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ
በውይይቱ ላይም ሌተናል ጄኔራል ሰለሞን አሸባሪው ሸኔ በመከላከያ ሠራዊታችን የማያዳግም ምት ዛሬ በየትኛውም መመዘኛ የኢትዮጵያ ስጋት እንዳይሆን መደረጉን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የሃይማኖትና የብሔር ብዝሃነት ያለ ልዩነት የሚስተናገድባት ህዝቦቿ በየ ባህላቸው ተከባብረው በአንድነት የሚኖሩባት ሃገር መሆኗን አንስተዋል።
ሌተናል ጄኔራል ሰለሞን አያይዘውም ህዝባችንን በማጋጨት የሃገራችንን ሠላም ለማደፍረስ በአሸባሪዎች የሚጠነሰሱ ሴራዎች አይሳኩም ብለዋል።
የአርሲ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኢብራሂም ከድር ከመከላከያ ሠራዊታችን ጋር እጅ እና ጓንት ሆነን የዞናችን ሠላም በጥፋት ሃይሎች እንዳይደፈርስ በተለይም አሸባሪው ሸኔን ከምንጩ ለማድረቅ ህብረተሰባችንን ባሳተፈ መልኩ ውጤታማ ስራዎች ማከናወናችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
የዞኑ የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ጀማል ገናሌ ዕዙ ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ ባደረጋቸው ዘመቻዎች አሸባሪው ሸኔ መደምሰሱን ጀሌዎቹም ከበርካታ ኤግዚቢቶች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸው አሁን ላይ በአርሲ ዞን አንፃራዊ ሠላም መኖሩን መግልጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።