ቀጥታ፡

በብሔረሰብ አስተዳደር ደጋፍ ለሚሹ አርሶ አደሮች ከሶስት ሺህ 800 ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ድጋፍ መደረጉ ተገለጸ

ሰቆጣ ፤ ሰኔ 18 ቀን 2016 (ኢዜአ) ፡-  በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር  ድጋፍ ለሚሹ  አርሶ አደሮች 55 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ከሶስት ሺህ 800 ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ድጋፍ መደረጉ ተገለጸ። 

ድጋፉን ያደረገችው የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን  ተወካይ አቶ መርሻ አንተነህ በርክክቡ ወቅት እንዳሉት፤  በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግር  ለተጎዱ ወገኖችን መደገፍ ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው። 

በብሄረሰብ አስተዳደሩ በተፈጥሮ ችግር ምክንያት ለተጎዱ አርሶ አደሮች የሚውል  55 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ሶስት ሺህ 889 ኩንታል የጤፍ ፣ስንዴ፣ ማሾና እንቁ ዳጉሳ ምርጥ ዘር ድጋፍ ማመቻቸታቸውን አሰታውቀዋል። 

በቀጣይም የጓሮ አትክልት ዘር እንደሚያቀርብ ጠቁመዋል። 

የተደረገው የምርጥ ዘር ድጋፍ  በተፈጥሮ ችግር ለተጎዱ  47 ሺህ 712 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ያሉት ደግሞ የብሄረሰብ አስተዳደሩ ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ አዲስ ወልዴ ናቸው። 

የምርጥ ዘር ድጋፉ አርሶ አደሩ ማሳውን በወቅቱ በዘር ለመሸፈን የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም