ቀጥታ፡

ኢንስቲትዩቱ በትግራይ ክልል ለአርሶ አደሮች አገልግሎት የሚውሉ 22 የእርሻ ትራክተሮችን አስረከበ

መቀሌ፤ ሰኔ 18/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት  22 የእርሻ ትራክተሮችን ለትግራይ ክልል  ጊዜያዊ አስተዳደር እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ  አስረከበ ።

በኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የትግራይ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አብረሀ ኪዳነማሪያም (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት ፣ ትራክተሮቹ በ71 ሚሊዮን ብር የተገዙ ናቸው ።

ትራክተሮቹ እያንዳንዳቸው ማረሻና መከስከሻ ማካተታቸውን ጠቅሰው፤   85 የፈረስ ጉልበት ያላቸው መሆናቸውን ተናግረዋል።

ትራክተሮቹ በክልሉ ስድስት ወረዳዎች በኩታገጠም ለተደራጁ አርሶ አደሮች በረዥም ጊዜ ብድር የሚሰጡ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ትራክሮቹን የተረከቡት በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ሀላፊ  እያሱ አብርሃ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ትራክተሮቹ  የክልሉ እርሻ ለማዘመን የጎላ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም