ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ቆይታቸውን ያጠናቀቁትን የዩኒዶ የኢትዮጵያ ተወካይ አሰናበቱ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ቆይታቸውን ያጠናቀቁትን የዩኒዶ የኢትዮጵያ ተወካይ አሰናበቱ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 18/2016(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ቆይታቸውን ያጠናቀቁትን የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) የኢትዮጵያ ተወካይ ካላብሮ አውሬሊያ ፓትሪዚአን አሰናበቱ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የዩኒዶ ተወካይዋ የኢትዮጵያ እውነተኛ ወዳጅ እንደነበሩ ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቅ በመረዳት ለሀገሪቱ ልማት በቁርጠኝነት መስራታቸውን ጠቅሰው፤ በቀጣይ የስራ ሕይወታቸው የተቃና እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።