በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው - ኢዜአ አማርኛ
በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 18/2016 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ20 ኪሎ ሜትር የሴቶችና ወንዶች እርምጃ ውድድር አትሌት ስንታየሁ ማስሬ እና አትሌት ምስጋና ዋቁማ ድል ቀንቷቸዋል።
በካሜሩን ዱዋላ እየተካሄደ የሚገኘው ሻምፒዮና 5ተኛ ቀን ውሎ በተለያዩ ውድድሮች በመሳተፍ ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።
በ20 ኪሎ ሜትር እርምጃ ሴቶች ውድድር ስንታየሁ ማስሬ በአንደኝነት ስታጠናቅቅ በተመሳሳይ አትሌት ምስጋና ዋቁማ በወንዶች ውድድር በአሸናፊነት ማጠናቀቁን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመለክታል።