የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ7ኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ7ኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ ሆነ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 17/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኢንዱስትሪው የአቪዬሽን ኦስካር ተብሎ በሚጠራው የስካይትራክስ መድረክ ለሰባተኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመባል ክብርን ተቀዳጅቷል።
አየር መንገዱ ከዚህ በተጨማሪ፦
የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክፍል አየር መንገድ ለስድስተኛ ተከታታይ ዓመት
የአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክፍል አየር መንገድ ለስድስተኛ ተከታታይ ዓመት፣ እንዲሁም
በአፍሪካ የኢኮኖሚ ክፍል ምርጥ ምግብ አገልግሎት ሰጪ አየር መንገድ በመባል ተደራራቢ ድልን መጎናጸፉን በመግለጽ በስኬቶቹ ሁሉ አብረውት ለተጓዙ ደንበኞቹ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ምስጋናውን አቅርቧል ።