በሀረሪ ክልል የ6ተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና መሰጠት ተጀምሯል - ኢዜአ አማርኛ
በሀረሪ ክልል የ6ተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና መሰጠት ተጀምሯል
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 17/2016(ኢዜአ)፦ በሀረሪ ክልል የ6ተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ይገኛል።
ፈተናው በ16 የገጠር እና 13 ከተማ በድምሩ በ29 የፈተና ጣቢያዎች እየተሰጠ መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ከ76 ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 5ሺህ 350 ተማሪዎች ለፈተናው መቀመጣቸውን የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ መግለጻቸውም ተጠቁሟል።
ተማሪዎቹን ለፈተናው ብቁ ለማድረግ የማጠናከሪያ ትምህርት ከመስጠት ጀምሮ የተለያዩ ፈተናዎችን በመስራት እንዲለማመዱ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱም ተገልጿል።
የትምህርት ጥራትን ወደ ተሻለ ደረጃ በማሳደግ እና ተማሪዎችን በማብቃት ኩረጃን የሚፀየፍ ትውልድ ለማፍራት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተጠቅሷል።
ለዚህ ጥረት ውጤታማነትም የተማሪ ወላጆችም ሆኑ ማህበረሰቡ የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ ቢሮ ሀላፊው ጥሪ ማስተላለፋቸውም እንዲሁ።
በዛሬው ዕለት ለፈተና የተቀመጡ ተፈታኞች 2ሺህ 917 ወንዶች እና 2ሺህ 433 ሴቶች በድምሩ 5ሺህ 350 ተማሪዎች መሆናቸው ተመላክቷል።