ቀጥታ፡

በአማራ ክልል ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የሚያስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ

ባህርዳር፤ ሰኔ 16 / 2016(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የሚስችሉ  ተግባራት በትኩረት  እየተከናወኑ   እንደሚገኙ  የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ገለጸ።

ቢሮው የ100 ቀናት እቅዱን ለማሳካት ያደረገውን የመስክ ድጋፍ፣ ክትትልና ቀጣይ አቅጣጫ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በባህር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው።


 

በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የአማራ ክልል የአስተዳደር  ዘርፍ አስተባባሪና የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው በመድረኩ ላይ እንዳመለከቱት፤የክልሉን ሰላም ለማስከበር የፀጥታ ሀይሉን አደረጃጀት እንዲያጠናክር የአመራር ቡድን ተልኮ ወስዶ ሲሰራ ቆይቷል።

በዚህም  የክልሉ ሰላም መሻሻል እያመጣ  መሆኑን ጠቅሰው፤ በክልሉ ሰላምን ዘላቂ ለማድረግ  የሚያስችሉ ተግባራት  አሁንም በትኩረት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

የዛሬው መድረክ ቡድኑ በሚያቀርበው የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ  ተመስርቶ በየደረጃው ያለው የፀጥታ መዋቅር ያለበትን ቁመና በመገምገም መልካም ተሞክሮን ለማስፋት ቀጣይ አቅጣጫ የሚቀመጥበት  መሆኑን አስረድተዋል።

እንዲሁም ችግሮችን በመፍታት የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጡ ተግባራትን ለማመቻቸትም እንዲሁ። 

በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ለሰላምና መልካም አስተዳደር ስራዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠርም ያለመ መድረክ ነው ብለዋል። 

በመድረኩ  የሚገኙ ግብአቶችን በመጨመር ለቀጣይ ስራዎች  ዝግጅት እንደሚደረግ  አብራርተዋል።

በመድረኩ ላይ  የክልሉ ከፍተኛ የፀጥታ ዘርፍ አመራር አባላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም