ቀጥታ፡

ይጠቅመናል፣ ይበጀናል የምንላቸውን ተወዳዳሪዎች መርጠናል - በአፋር ክልል ድምፃቸውን የሰጡ መራጮች

ሠመራ፤ ሰኔ 16/2016 (ኢዜአ)፦ ይጠቅመናል ይበጀናል የምንላቸውን ተወዳዳሪዎች መርጠናል ሲሉ በአፋር ክልል ተላላክ ምርጫ ክልል በነማለፈን ምርጫ ጣቢያ ድምፃቸውን የሰጡ መራጮች ተናገሩ።

በአፋር ክልል ምርጫ ከሚካሄድባቸው አንዱ የተላላክ ምርጫ ክልል፣ ነማለፈን ምርጫ ጣቢያ ሲሆን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሪፖርተር በጣቢያው ተገኝቶ እንደተመለከተው ምርጫው ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እየተካሄደ ነው።

ኢዜአ ካነጋገራቸው መራጮች መካከል አቶ ሐመዱ ሐመድ፤ ዛሬ እየተካሄደ ባለው ምርጫ መሳተፋቸውን ገልፀው፤ ዛሬ ይጠቅመናል የምንለውን የመረጥንበት በመሆኑና ይህም በመከናወኑ ደስተኞች ነን ብለዋል።

አቶ ሰኢድ ሐሰን በበኩላቸው እንደተናገሩት በዚህ ምርጫ ይጠቅመኛል የምለውን የምመርጥበት በመሆኑና አንድ ድምፅ ዋጋ ስላለው መጥቼ ተሳትፌያለሁ ብለዋል።

ወይዘሮ ፋጡማ ሐመድ ዊቲካም እንደተናገሩት፤ ዛሬ በነማለፈን ምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ይጠቅመኛል ያሉትን መምረጣቸውን ተናግረዋል።

ዛሬ በተላላክ የምርጫ ክልል ነማለፈን የምርጫ ጣቢያ ያለው የምርጫ ሂደት ሰላማዊ በሆነ መልኩ በመከናወን ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም