ቀጥታ፡

በሶማሌ ክልል ጅግጂጋ ከተማ ድጋሚ ምርጫ መካሄድ ጀመረ

ጂግጂጋ፤ ሰኔ 16/2016(ኢዜአ)፦ በሶማሌ ክልል ጅግጂጋ ከተማ ድጋሚ ምርጫ በየምርጫ ጣቢያዎች የምዝገባና የድምፅ አሰጣጡ ሂደት እየተካሄደ ነው።

የምዝገባና የድምፅ አሰጣጡ ሂደት ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።

በጂግጂጋ ከተማ ምርጫ ክልል ሁለት ድጋሚ ምርጫ የድምፅ አሰጣጡ የተጀመረው ታዛቢዎች በተገኙበት የድምፅ መስጫ ኮሮጆዎች እና ሌሎች ለምዝገባና ድምፅ አሰጣጥ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች መሟላታቸው ተረጋግጦ ነው።


 

የኢዜአ ሪፖርተሮች በማለዳ በከተማዋ ተዘዋውረው እንደተመለከቱት፤ ህዝቡ በየምርጫ ጣቢያዎቹ በመገኘት እየተመዘገበና ድምፁን እየሰጠ ይገኛል።

በጅግጅጋ ከተማ ምርጫ ክልል ሁለት ህዝቡ ድምፁን የሚሰጥባቸው 123 የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን ህዝቡ እየመረጠ ያለው ለክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩ ዕጩዎችን መሆኑን የምርጫው አስተባባሪ አቶ ሀይለየሱስ ወርቁ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በዛሬው እለት በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ምርጫ ክልል ሁለት አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሶስት የግል ተወዳዳሪዎች በምርጫው ይወዳደራሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም