በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ድጋሚ ምርጫ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ድጋሚ ምርጫ እየተካሄደ ነው

አሶሳ፤ ሰኔ 16/2016(ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች ድጋሚ ምርጫ እየተካሄደ ነው።
የአትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሪፖርተር በከተማው የአሶሳ ሆሀ እና አሶሳ መገሌ ምርጫ ክልሎችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል።
በዚህም በየምርጫ ጣቢያዎቹ ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ህዝቡ ድምጽ መስጠት መጀመሩን መመልከት ተችሏል።
የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ከመጀመሩ በፊት ኮሮጆዎች ባዶ መሆናቸው፣ የምስጢር ድምጽ መስጫ ክፍሎች ድምጽ ለመስጠት ምቹ መሆናቸው ታውቋል።