ቀጥታ፡

የመስቃን ወረዳ እና ማረቆ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች የድጋሚ ምርጫ ድምጽ መስጠት ጀመሩ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 16/2016(ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመስቃን ወረዳ እና ማረቆ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች ከማለዳው ጀምሮ የድጋሚ ምርጫ ድምጽ መስጠት ጀምረዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ኛው ሀገራዊ የድጋሚና ቀሪ ምርጫ የማስፈጸሚያ ቁሳቁሶችን በማሟላት ዛሬ ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ለማካሄድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ይታወሳል።

በዚህም የድጋሚና ቀሪ ምርጫው በዛሬው ዕለት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በ29 የምርጫ ክልልና በ1 ሺህ 258 የምርጫ ጣቢያ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።


 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመስቃን ወረዳ እና ማረቆ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎችም ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ በድምጽ መስጫ የምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምፃቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

ኢዜአ በመስቃን ወረዳ እና ማረቆ ልዩ ወረዳ ተዘዋውሮ ባደረገው ምልከታም ነዋሪዎቹ በ6ኛው ሀገራዊ የድጋሚ ምርጫ ድምፃቸውን እየሰጡ እንደሚገኙ አረጋግጧል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ2013 እና በ2014 ዓ.ም በሁለት ዙሮች ሀገራዊ ምርጫ ያካሄደ ሲሆን በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ወቅት የጸጥታ እና የተዓማኒነት ችግር በነበረባቸው አካባቢዎች ድጋሚና ቀሪ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን ይታወሳል።

 

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም