ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ28ኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻል ሲዳማ ቡናን አሸነፈ 

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 15/2016 (ኢዜአ)፡-በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ28ኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻል ከሲዳማ ቡና ጋር ያደረገውን ጨዋታ 4 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ።

በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ለመቻል ጎሎቹን ምንይሉ ወንድሙ በፍፁም ቅጣት ምት በ42ተኛው ደቂቃና፤ በኃይሉ ግርማ በ47ተኛው ደቂቃ እንዲሁም ከነዓን ማርክነህ በ73ተኛው ደቂቃ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

የሲዳማ ቡናን ብቸኛ ጎል ብርሃኑ በቀለ በ65ተኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።  

ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ መቻል 2 ለ 1 ማሸነፉ ይታወሳል።

መቻል የዛሬውን ጨዋታ በማሸነፉ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በነገው ዕለት ጨዋታውን እስከሚያደርግ፤ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር እኩል 57 ነጥብ ይዟል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ28ኛ ሳምንት መርሐ ግብር፤ በነገው ዕለት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ሀምበሪቾ ከወላይታ ዲቻ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጠናቀቃል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም