ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የአረንጓዴ ዓሻራ ቅድመ መክፈቻ መርሃ ግብር ተካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የአረንጓዴ ዓሻራ ቅድመ መክፈቻ መርሃ ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 14/2016(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ዛሬ የአረንጓዴ ዓሻራ ቅድመ መክፈቻ መርሃ ግብር ተካሄደ።
ኢትዮጵያ ላለፉት አምስት አመታት በ2011 ዓመተ ምህረት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተጠነሰሰው የአረንጓዴ ዓሻራ መርሃ ግብር አማካኝነት በየአመቱ የችግኝ ተከላ ስራ ስታካሂድ መቆየቷ ተገልጿል።
ዛሬ የባለፉት አመታት ጥረታችንን በማጤን የ2016ቱን ዙር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ቅድመ ጅማሮ መርሃ ግብር ተካሄዷል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በተካሄደውም የአረንጓዴ ዓሻራ ቅድመ መክፈቻ መርሃ ግብር ሁነት የኢትዮጵያ የደን ሽፋን ሪፖርት ይፋ ሆኗል።
በመቀጠልም የሀገራዊውን የአረንጓዴ አሻራ ይዘት እና የስራ ውጤት በሰዋዊ ተረክ የሚያቀርብ አለምአቀፍ ዘጋቢ ፊልም የምረቃ እይታ ተካሂዷል።
ይፋ የተደረገው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን ሪፖርት እንዳመለከተው የደን ሽፋናችን በ2011 ዓመተ ምህረት ከነበረበት 17.2 በመቶ ወደ 23.6 በመቶ ከፍ ብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በመርሃ ግብሩ ባደረጉት ንግግር ይህን የዕድገት ውጤት ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።