ቀጥታ፡

በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ኢትዮጵያ የወርቅና የብር ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 14/2016(ኢዜአ)፦ በካሜሩን ዱዋላ ከተማ ዛሬ መካሄድ በጀመረው 23ኛ የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያ የወርቅና የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።

በውድድሩ አትሌት ፋንታዬ በላይነህ እና አትሌት ውብርስት አስቻለ ተከታትለው በመግባት ለሀገራቸው የወርቅና የብር ሜዳሊያ ማምጣታቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም